Posts

ሚዲያን መቆጣጠር ሀገርን መቆጣጠር ነው» ክፍል 2

Image
 «ሚዲያን መቆጣጠር ሀገርን መቆጣጠር ነው»  ክፍል 2: በኡስታዝ አሕመዲን ጀበል ❄❄❄❄❄❄❄❄❄❄❄❄❄❄❄❄ የሀገራችንን የአማርኛ ሚዲያዎች ተቆጣጥረው እንዳሻቸው የሚዘውሩት የሰጠመችው ደሴት ናፋቂዎች «ሚዲያን መቆጣጠር ሀገርን መቆጣጠር ነው»  የሚል ሰነድ በማጋራትና ይህንኑ መነሻ በማድረግ በእኔ ላይ ከጀመሩት የስም ማጥፋት ዘመቻ ጋር ተያይዞ ንጹሃንና የዋሆችን ለመታደግ ስል ብቻ በርዕሰ ጉዳዩ ላይ ሀሳቤን እያጋሯኋችሁ እገኛለሁ።  በክፍል አንድ በርካታ ነጥቦችን ዳሰናል። በዚህ ክፍል ደግሞ «ሚዲያን ስለመቆጣጠር» ጉዳይና ስለስልጠናው አብረን እንመለከታለን። ሀሳቡ ለሌሎች እንዲደርስ በማንኛውም መንገድ ሼር በማድረግ የበኩልዎን ሚና እንዲወጡ እየጋበዝኩ ሀሳቤን እቀጥላለሁ። ✺✺✺✺✺✺✺✺✺✺✺✺✺✺✺✺ «ጠንቃቃ ካልሆንክ ጋዜጦች የተበደሉትን እንድትጠላና በዳዮችን እንድትወድ ሊያደርጉህ ይችላሉ።» (ማልኮም ኤክስ) ✸✸✸✸✸✸✸✸✸✸✸✸✸✸✸✸✸ «ሚዲያን መቆጣጠር ሀገርን መቆጣጠር ነው» የሚለውን ቁንጽል ሀሳብ ይዘው እንደነውር ለማሳየት የሚጥሩት አካላት ሆን ብለው የዘነጉት ነገር እንዳለ እናስተውል። የሰውን ሐሳብ ለመቆጣጠር (ማኑፑሌት ለማድረግ) በሚጥሩ ሚዲያዎች መካከል ማህበረሰቦች ራሳቸውን ሊከላከሉና የሚዲያ ጥምዘዛን ሊቋቋሙ የሚችሉት ጠንካራ ሚዲያ ሲኖራቸው ነው። ከዚህ አንጻር «ሚዲያን መቆጣጠር ሀገርን መቆጣጠር ነው» የሚለው ንግግር የሚዲያን ኃይል ማስጠንቀቂያ እንጂ የግድ ሰዎችን የመቆጣጠር ሙከራ ነው ማለት አይደለም።   ሚዲያዎችን በመቆጣጠር የህዝብን አመለካከት የመቆጣጠሩ ፋሽን ምን ያክል ተጨባጭ እውነታ እንደሆነ ለማየት ጥሩ ምሳሌ የሚሆነን የአሜሪካ ሚዲያዎችን በባለቤትነት የተቆጣጠሩት አካላት ማንነት ነው። በ...

ሚዲያን መቆጣጠር ሀገርን መቆጣጠር ነው

Image
 «ሚዲያን መቆጣጠር ሀገርን መቆጣጠር ነው» በአሕመዲን ጀበል ክፍል አንድ 📻📻📺📺📡📡📢📢🔊🔊🔊📱📱🎤🎤📹 «በምድር ላይ እጅግ አደገኛው ነገር መገናኛ ብዙሃን(ሚዲያ) ነው።የብዙሃኑን አእምሮ ስለሚቆጣጠሩ ንፁሀንን ጥፋተኛ ፣ጥፋተኛውን ደግሞ ንፁህ የማድረግ አቅም አለው። ይህም ኃይል ነው።» (ማልኮም ኤክስ)  💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥 እንኳንስ በዚህ ዘመን ያኔ ጥንትም ቢሆን ኋላ ቀርና ልትወገድ ተገቢ በመሆኗ የሰጠመችውን ደሴት ከባህሩ ዉስጥ ፈልገው ዳግም ሊያቆሟት እየተጉ ያሉ «የሰመጠችው ደሴት ናፋቂዎች» እኔን «እንቅፋት ሆነብን» ብለው በማሰብ  በማሳጣትና በማሸማቀቅ አፍ የሚያዘጉበት አንዳች ማስረጃ ብናገኝ ብለው ማስረጃ ፍለጋ ብዙ ለፍተዋል።እየለፉም ነው። እስካሁን አንዳች ለማጠልሸት የሚሆን ነገር በማጣታቸው ያለማስረጃ የማጠልሸቱ ጉዳይ በተለይ በሙስሊሙና ምክንያታዊ በሆኑት ክርስትያኖች ዘንድ ዳገት ሲሆንባቸው ዉንጀላቸውን በማስረጃ ማስደገፍ ከቻልን ብለው ብዙ ጥረዋል።እየጣሩም ይገኛሉ። የግል ኢሜይሎቼን ከአዲስ አበባ አምስት ኪሎ፥ከካዛንቺስ፥ ከአሜሪካ፥ከጀርመንና ከዱባይ ሀገር በተደጋጋሚ ጊዜ ለመጥለፍ ሞክረዋል። ተንቀሳቃሽ ስልኬንም አሰርቀዋል (ዘመናዊውን አይፎን ስልኬን የሰረቀው አካል ስልኬ እጁ ላይ እንደገባ ወዲያው ከስልኩ ይልቅ በስልኩ ላይ ተከፍተው (Signin) ሆነው የነበሩ የማህበራዊ ሚዲያና የኢሜይል ፓስወርዶቼን ለመለወጥና የራሱ ለማድረግ ሲታገል እንዲያሳውቀኝ ለጥንቃቄ  ያደረግኩት የሲስተሙ አላርም በሌላኘው ስልኬ ላይ «ፓስወርዶቹን ለመለወጥ የፈለግከው አንተ ነህን? » ሲል በጥያቄ እየተደረገ ያለውን ሙከራ አሳወቀኝ።እናም ጥረታቸውን ስንዝር ሳይጓዙ ተኮላሸ)። እስካሁን በዚህና በሌ...

ከታሪክ ማህደር ክፍል 1

Image
 ከታሪክ አለመማር ለውድቀት ይዳርጋል ★★★★★★★★★★★★★★★★ ‹‹ይገሰፁ ዘንድ ቃላችን እንዲደርሳቸው አድርገናል።›› (ቁርኣን 28÷ 51)                          ★★★  ታሪክ ዛሬ ላይ ሆነን የሰው ልጆችን የትላንት ሕይወትን እንድንመለከተው ይረዳናል፡፡ በመሆኑም ታሪክ እጅግ ጠቃሚ የዕውቀት ዘርፍ ነው፡፡ የሰው ልጆት ያለፉበትን ጐዳና፤ ታሪካዊ ክስተቶችን፤ የጥፋትና የልማት አብነቶችን ያሳውቀናል፡፡ ከእነሱ ታሪክም ለዛሬ ስንቅ የሚሆነንን በርካታ ቁም ነገሮችን እንቀስምበታለን፡፡ ከውድቀታቸው የውድቀትን ምክንያቶች እናውቅበታለን፡፡ ከስኬታቸውም የስኬትን ምስጢር እንማርበታለን፡፡ ከትግላቸው አዋጭ የሆነውን የትግል ስልት  እንለይበታለን፡፡ ጽናታቸው ደግሞ የጽናት አብነት ይሆነናል፡፡ ለአብነት ያክልም የዚህ መጽሐፍ ትኩረት የሆነውን የሙሳንና የፊርዐውንን ታሪክ እንመልከት፡፡ ከሁለቱ የትግል ታሪክ እስካሁን በርካታ ቁም ነገሮችን ጨብጠናል፡፡ ለአብነትም የሙሴ ጽናትን ተረድተናል፡፡ ታሪኩን በጥሞና ስናነበው ለኛም ጽናትን ይለግሰናል፡፡ ቁርኣንም ይህንኑ የሙሳን ታሪክ ጨምሮ የመልዕክተኞችን ሁሉ ታሪክ መተረኩ ጽናት እናገኝበት ዘንድ መሆኑን እንዲህ ይገልጸዋል፦        “ይህን ሁሉ (የቀደምት) መልዕክተኞች ታሪክ÷ በርሱ ልብህን ልናፀና ተረክንልህ፡፡…” (ሁድ÷ 120) ታሪክን ስንረዳ የማስተዋል አቅማችን ይጨምራል፡፡ ነገሮችን የማስተንተን ችሎታችን ይጐለብታል፡፡ የምናደምጠውን ነገር የምንረዳበት ዕድላችን ይልቃል፡፡ በመሆኑም የቀደምት ሕዝቦችን ታሪክ÷ የነገሥታቱን አሻራ እና ቅርሶችን ስንመለከት ዘ...

ፍልስፍና ክፍል 4

Image
 እርስዎ ቀድሞውኑ ፈላስፋ ነዎት! የፍልስፍና ፍላጎት ያላቸው ሰዎች ፈላስፋ ናቸው፤ ነገር ግን መጽሐፍትን ማንበብ እና ስለምታነበው ነገር ማሰላሰል እና ማሰብ ብዙ ያደርገዋል።  ሁላችንም ፈላስፎች ነን። ሁሉም ሰው ልዩ ነው። በሕይወታችን ውስጥ ያለፍንባቸው ነገሮች ፣ መሰናክሎች፣ ውድቀቶች እና በእነዚያ መሰናክሎች ላይ የምንሰራበት መንገድ፥ የራሳችንን ፍልስፍናዊ አስተሳሰባችንን ይቀርጻል፤ የተወሰነ ህይወት እና የተወሰኑ እምነቶች ያለው ሰው እንድንሆን ያደርጉናል። የፍልስፍና ትምህርህ ቤት አልገባሁም፤ አዎ ግን ፈላስፋ ነኝ። ፍልስፍና የጥበብ ፍቅር ነው ወይም የዕውቀት፣ የእውነታ እና የህልውና መሰረታዊ ተፈጥሮ ጥናት ነው ሊሉ ይችላሉ። ስለዚህ አዎ እኔ ለማለት የሞከርኩት ይህንኑ ነው። ክፍት አዕምሮ አለኝ፤ ለመማር ረሃብተኛ ነኝ፤ ከብዙ ሰዎች አመለካከቶችን ለማግኘት እፈልጋለሁ፤ ጥያቄዎችን ለመጠየቅ አልፈራም፤ በቀላል ቃላት የራሴ ልምዶች ፣ ምልከታዎች እና እውቀቶች ለእኔ ፍልስፍና ነው። ስለዚህ አዎ ፈላስፋ ነኝ!

ፍልስፍና ክፍል 3

Image
 ከሀሳብ የተሠራ ኃያል ሕዝብ! ሕዝቦች ሰለጠኑ ስንል በቀጥታ በፍልስፍና፣ በሳይንስና ጥበብ አደጉ ማለታችን ነው፡፡ እነዚህ ሶስት አንኳር የሰው ልጅ የመላቅ መስታወቶች ናቸው፡፡ ስልጣኔዎችን ማጥናት ማለት በሌላ መልኩ እነዚህን ጉዳዮች ማጥናት እንደማለት ነው፡፡ ግሪክ ስንል ሶፉክልስ፣ አሪስቶትል፤ አርኪሜድስ… የሚሉ አሳቢዎችን እናጠናለን፡፡ የዓረብ ስልጣኔ ስንል አልኸዋሪዝሚ፣ ኢብን ሲና፣ አልገዛሊ …የሚሉ አሳቢዎችን እናጠናለን፡፡ ፈረንሳይ ስንል ዴካርት፣ ሩሶ፣ ቮልቴር… የሚሉ አሳቢዎችን እናነባለን….ወዘተ። ሌላውም ስልጣኔ እንዲሁ ነው፡፡ ስልጣኔ ስላላቸው ሕዝቦች ማጥናት ማለት ታላላቅ ፈላስፎችን፣ ሳይንቲስቶችንና ከያንያንን ማጥናት እንደማለት ነው፡፡ በልማድ፣ በኃይማኖት፣ በብሔር ማንነታቸው ብቻ የሰለጠኑ ሕዝቦችን ከታሪክ ገጽ አናገኝም፡፡ ልማዶች (ባህል፤ ኃይማኖት፣ ወግ ) የአንድ ሕዝብ የሞራል መልኮች ናቸው፡፡ የጋራ ጠባይን ይገልጻሉ፡፡ ለስልጣኔ ብልጽግና አሻራ አላቸው፡፡ ህብረትን በማጽናት የሞራል ባህልን ለመፍጠር ያግዛሉ።   #የዘር_ካርድ በፈላስፋ እና ደራሲ ቡርሐን አዲስ

ፍልስፍና ክፍል 2

Image
 ፈላስፋ አዋቂ አይደለም፤ የእውቀት ወዶ ዘማች እንጂ። የፊዚክስ ሊቅ ስለ ፊዚክስ ህግጋት ጠንቅቆ ማወቅ ይጠበቅበታል። የህክምና ሰው ተጠብቦ ማዕረግን ይቀዳጃል፤ የእውቀቱን ልክ ሲያደረጅ ሊቅነቱ ይታወጅለታል። በፍልስፍና መልክዓምድሩ ቅጣምባሩ ሌላ ነው። ፈላስፋ ጥቅጥቅ ባሉ የኃሳብ መንገዶች ነጉዶ ያገኘውን ሁሉ ሊያሰላስል የቆረጠ መርማሪ ነው፤ አንዳች የሙያ ሰገነትን እንዲቆናጠጥ የማይጠበቅ። በጥያቄ እና በፍተሻ ጉዞው መጨረሻ የሆነ ለምለም መስክ ባያገኝ ግድ የለውም፤ ጉዳዩ ጉዞው ነው። ከማሰቡ ነው እንጂ አስቦ በስተመጨረሻ ከሚደርስበት መደምደሚያ አይደለም፤ መጨረሻ ላይኖረው ይችላል። በአንድ ሰው መቃብር ላይ የተጻፈ! ወጣት ሳለሁ ምናቤ ገደብ በሌለው ወቅት ፥ ዓለምን ስለ መለወጥ አልም ነበር። እያደኩና እየበሰልኩ ስመጣ ግን ፥ ዓለምን መለወጥ እንደማልችል ተረዳሁ። ከዚያም ምኞቴን አጠር አደረኩና ሀገሬን ለመለወጥ ወሰንኩ። ነገር ግን እሱም የሚሳካ አልሆነም። ወደ እድሜዬ መጨረሻ እየደረስኩ ስመጣ ፥ አንድ ሙከራ ለማድረግ ወሰንኩ፤ ይኽም የራሴን ቤተሰብ እና ለኔ ቅርብ የሆኑትን ለመለወጥ ወሰንኩ፤ እሱም አልሆነም። በዚኽች ምድር ላይ የነበረኝ ቆይታ ሲገባደድ የመጨረሻዋ ሰዓት ላይ ፥  አልጋዬ ላይ ተጋድሜ ድንገት ይህንን  አስተዋልኩ፤ ራሴን ለውጬ ቢሆን ኖሮ ቤተ-ሰቤን መለወጥ እችል ነበር። ከዚያም ሀገሬን የተሻለች ማድረግ እችል ነበር። ማን ያውቃል ዓለምንም መቀየር እችል ይሆን ነበር! እናስ?! እናማ ለውጥን ከራስህ ጀምር!

ፍልስፍና ክፍል 1

Image
 በ1902 አንድ ፕሮፌሰር ተማሪውን "ይህችን ዓለም ወይም ዮኒቨርስ የፈጠራት ፈጣሪ መሆን አለመሆኑን ማን ነው የሚነግረን?" ሲል ጠይቆ ነበር። ተማሪውም "አዎ ይኽችን ምድር የፈጠራት ፈጣሪ ነው" ሲል መልስ ሰጠ። መልሶ መምህሩ ሌላ ጥያቄ አቀረበ፤ "መልካም ሲዖልንስ የፈጠረው ማነው?"። ተማሪው ለአፍታ በዝምታ ማዕበል ተዋጠ፤ መልሶ ተማሪው አስተማሪውን ጠየቀ " ውድ መምህር እኔ ደግሞ መልሼ ልጠይቅዎት ፤ ቀዝቃዛ ነገር እዚህ ምድር ላይ አለ ብለው ያምናሉ ?"። "ይሄማ ምን ያጠያይቃል የብርድ ስሜት መኖሩ አይታወቅህም ?!" ሲሉ መምህር መልስ ሰጡ። ተማሪውም "መምህሬ ይቅርታ አድርጉልኝና ተሳስተዋል ፤ ቀዝቃዛ የሚባል ነገር የለም ፤ ብርድ ማለት የሙቀት እጥረት ነው ፤ ቅዝቃዜ ብሎ ነገር የለም "። ሲል ተማሪው ምላሽ ሰጠ። በድጋሚ ተማሪው ጥያቄ ማቅረቡ አልቀረም "ለመሆኑ መምህር ጨለማ አለ ብለው ያምናሉ?"። ፕሮፌሰርም "አዎ ጨለማ አለ" የሚል መልስ ሰጡ ። ተማሪውም  "ፕሮፌሰር በትልቁ ተሳስተዋል ፤ ጨለማ የሚባል ነገር የለም ፤ የብርሃን አለመኖር እንጂ፤ ሁልጊዜ የምንማረው ስለ ብርሃንና ስለ ሙቀት እንጂ ስለ ቅዝቃዜና ስለ ጨለማ አይደለም፤ ስለዚህም ሲዖል የለም። በመሰረቱ ሲዖል ማለት የፍቅር፣ የእምነት፣ በፈጣሪ የማመን እጥረት ማለት ነው" ብሎ ነበር ። ያ ተማሪ እውቁ ሳይንቲስት አልበርት አነስታይን ነው ። ፈላስፋው ነኝ