ፍልስፍና ክፍል 3
ከሀሳብ የተሠራ ኃያል ሕዝብ!
ሕዝቦች ሰለጠኑ ስንል በቀጥታ በፍልስፍና፣ በሳይንስና ጥበብ አደጉ ማለታችን ነው፡፡ እነዚህ ሶስት አንኳር የሰው ልጅ የመላቅ መስታወቶች ናቸው፡፡
ስልጣኔዎችን ማጥናት ማለት በሌላ መልኩ እነዚህን ጉዳዮች ማጥናት እንደማለት ነው፡፡ ግሪክ ስንል ሶፉክልስ፣ አሪስቶትል፤ አርኪሜድስ… የሚሉ አሳቢዎችን እናጠናለን፡፡ የዓረብ ስልጣኔ ስንል አልኸዋሪዝሚ፣ ኢብን ሲና፣ አልገዛሊ …የሚሉ አሳቢዎችን እናጠናለን፡፡ ፈረንሳይ ስንል ዴካርት፣ ሩሶ፣ ቮልቴር… የሚሉ አሳቢዎችን እናነባለን….ወዘተ።
ሌላውም ስልጣኔ እንዲሁ ነው፡፡ ስልጣኔ ስላላቸው ሕዝቦች ማጥናት ማለት ታላላቅ ፈላስፎችን፣ ሳይንቲስቶችንና ከያንያንን ማጥናት እንደማለት ነው፡፡
በልማድ፣ በኃይማኖት፣ በብሔር ማንነታቸው ብቻ የሰለጠኑ ሕዝቦችን ከታሪክ ገጽ አናገኝም፡፡ ልማዶች (ባህል፤ ኃይማኖት፣ ወግ ) የአንድ ሕዝብ የሞራል መልኮች ናቸው፡፡ የጋራ ጠባይን ይገልጻሉ፡፡ ለስልጣኔ ብልጽግና አሻራ አላቸው፡፡ ህብረትን በማጽናት የሞራል ባህልን ለመፍጠር ያግዛሉ።
#የዘር_ካርድ
በፈላስፋ እና ደራሲ ቡርሐን አዲስ
Comments
Post a Comment