ፍልስፍና ክፍል 1
በ1902 አንድ ፕሮፌሰር ተማሪውን
"ይህችን ዓለም ወይም ዮኒቨርስ የፈጠራት ፈጣሪ መሆን አለመሆኑን ማን ነው የሚነግረን?" ሲል ጠይቆ ነበር።
ተማሪውም "አዎ ይኽችን ምድር የፈጠራት ፈጣሪ ነው" ሲል መልስ ሰጠ።
መልሶ መምህሩ ሌላ ጥያቄ አቀረበ፤ "መልካም ሲዖልንስ የፈጠረው ማነው?"።
ተማሪው ለአፍታ በዝምታ ማዕበል ተዋጠ፤ መልሶ ተማሪው አስተማሪውን ጠየቀ " ውድ መምህር እኔ ደግሞ መልሼ ልጠይቅዎት ፤ ቀዝቃዛ ነገር እዚህ ምድር ላይ አለ ብለው ያምናሉ ?"።
"ይሄማ ምን ያጠያይቃል የብርድ ስሜት መኖሩ አይታወቅህም ?!" ሲሉ መምህር መልስ ሰጡ።
ተማሪውም "መምህሬ ይቅርታ አድርጉልኝና ተሳስተዋል ፤ ቀዝቃዛ የሚባል ነገር የለም ፤ ብርድ ማለት የሙቀት እጥረት ነው ፤ ቅዝቃዜ ብሎ ነገር የለም "። ሲል ተማሪው ምላሽ ሰጠ።
በድጋሚ ተማሪው ጥያቄ ማቅረቡ አልቀረም "ለመሆኑ መምህር ጨለማ አለ ብለው ያምናሉ?"።
ፕሮፌሰርም "አዎ ጨለማ አለ" የሚል መልስ ሰጡ ።
ተማሪውም "ፕሮፌሰር በትልቁ ተሳስተዋል ፤ ጨለማ የሚባል ነገር የለም ፤ የብርሃን አለመኖር እንጂ፤
ሁልጊዜ የምንማረው ስለ ብርሃንና ስለ ሙቀት እንጂ ስለ ቅዝቃዜና ስለ ጨለማ አይደለም፤ ስለዚህም ሲዖል የለም። በመሰረቱ ሲዖል ማለት የፍቅር፣ የእምነት፣ በፈጣሪ የማመን እጥረት ማለት ነው" ብሎ ነበር ።
ያ ተማሪ እውቁ ሳይንቲስት አልበርት አነስታይን ነው ።
ፈላስፋው ነኝ
Comments
Post a Comment