ማስታወቂያ

 ማስታወቂያ 

🌷🌷🌷🌷


በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሃጅና ዑምራ ዘርፍ የ1444 ሃጅ መስተንግዶ አካል የሆነው የሃጃጆች መዲና እና መካ የማረፊያ (ሆቴልና) ምግብ አማራጮችን በማጥናት ላይ ይገኛል። 


በመሆኑም በመስኩ ከሳዑዲ ዓረቢያ የሃጅና ዑምራ ሚኒስቴር ጨምሮ ከሚመለከታቸው አካላት አግባብ ያለው የታደሰ ፈቃድ ያላችሁ አቅራቢዎች በሚከተሉት መስፈርት የምታሟሉ ከታች በተመለከተው አድራሻ የአቅርቦት ቴክኒካል ፕሮፖዛል (ዋጋ ሳይጨምር) እንድታስገቡ ተጋብዛችኋል።


ሆቴል

🔴🔴


የሃጅና ዑምራ ሚኒስቴር መሰረታዊ መስፈርቶችን በተለይም የመብራት፣ የውኋ፣ የፍሪጅ፣ የፅዳት፣ የአየር ማቀዝቀዣ እና የመሳሰሉት ያልተቋረጠ አገልግሎት  የሚያሟሉ ሆነው 


*ሀ. ሆቴል በመዲና*

 🏵🏵🏵🏵🏵🏵

አቅም: በድምሩ ከ3,000  እስከ 3,500 ያላነሱ ሁጃጆችን ባንዴ የሚያስተናግዱ ከ2 እስከ 4 ህንፃዎች በአንድ አካባቢ ያሉት

ቦታ: ከመርከዚያ (ሃረም ዙሪያ ካሉት ሆቴሎች) ውጭ

ተጨማሪ: በሃረም እና በሆቴሉ ዙሪያ ፈጣን መንገድ የሌለው

ርቀት: ከሃረም በእግር ከ15 ደቂቃ ርቀት በላይ (1.5 ኪሜ) ያልሆነ

የመመገቢያ አዳራሽ ያለው (300 ሰው በአንድ ህንፃ)

የመቀበያ ቦታ Reception ላይ ሰፊ ማረፊያ ወይም ማቆያ ያለው 

በአቅራቢያው የሱቅ፣ ፋርማሲ እና መስጊድ አገልግሎት ያለው


*ለ. ሆቴል በመካ*

🔺🔺🔺🔺🔺🔺

አቅም: በአንድ ማዕከል የተለያዩ ሕንፃዎች ድምሩ ከ3 ሺ ያላነሱ ሁጃጆችን ባንዴ የሚያስተናግዱ ህንፃዎች በአንድ አካባቢ ያሉት

ቦታ: ከመርከዚያ ውጭ የሆነ

ተጨማሪ: በሃረም እና በሆቴሉ ዙሪያ ፈጣን የአገር አቋራጭ መንገድ የሌለው

ርቀት: ከሃረም ከ3 ኪ.ሜ ያልበለጠ

መሰረታዊ አገልግሎት: የልብስ ማጠቢያ ያለው

የመመገቢያ አዳራሽ ያለው (500 ሰው በአንድ ህንፃ)

የመቀበያ ቦታ Reception ላይ ሰፊ ማቆያ ወይም ማረፊያ ያለው

በአቅራቢያው የሱቅ እና መስጊድ አገልግሎት ያለው

አቅጣጫ: በምዕራብ ወይም ሰሜን ምዕራብ በኩል (የጅዳ መግቢያ ወይም ወደ መዲና መውጫ) ቢሆን ይመረጣል

ለእያንዳንዱ አልጋ የነፍስ ወከፍ  ሶኬት ያለው

ለህንፃው ያልተቋረጠ የጥገና አገልግሎት መስጠት

የሽንት ቤት ከፈረንጆቹ በተጨማሪ የቱርክ (የአረብ) የመሬት አይነት ያለው

ህንፃው የአውቶቡስ መሳፈሪያ ተጨማሪ ቦታ ያለው ቢሆን ይመረጣል።

 

*ሐ. የምግብ አገልግሎት በመካ እና በመዲና*

💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧

 1. አስፈላጊ ፍቃዶች እና መሳሪያዎች የተገጠመላቸው ኩሽናዎች

2. እጅግ በጣም ጥሩ ቅልጥፍና እና ከፍተኛ መጠን የማቅረብ አቅምና ልምድ ያለው

3. በኢትዮጵያ ሀጅ ጉዳይ ጽ/ቤት ጥያቄ መሰረት የምግብ ሜኑ ለማቅረብ ሙሉ በሙሉ ዝግጁ የሆነ


በመሆኑም ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ ህጋዊ አቅራቢዎች ይህንን የሚያስረዳ ማስረጃዎቻችሁን ፕሮፖዛል በሚቀጥሉት አድራሻዎች ከጥር 6 ጀምሮ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን ።


ኢ_ሜይል: mailtomajlis@gmail.com 


ዌብሳይት: https://ethiopianmajlis.org.et/service-provider-registration


Comments

Popular posts from this blog

ከታሪክ ማህደር ክፍል 1

Seenaa Motummaa Jimmaa (kutaa 1ffaa)

The Untold Story of the Battle of Maqdala and the Struggle Between Emperor Tewodros and the Oromos