ፍልስፍና ክፍል 2

 ፈላስፋ አዋቂ አይደለም፤ የእውቀት ወዶ ዘማች እንጂ። የፊዚክስ ሊቅ ስለ ፊዚክስ ህግጋት ጠንቅቆ ማወቅ ይጠበቅበታል። የህክምና ሰው ተጠብቦ ማዕረግን ይቀዳጃል፤ የእውቀቱን ልክ ሲያደረጅ ሊቅነቱ ይታወጅለታል።

በፍልስፍና መልክዓምድሩ ቅጣምባሩ ሌላ ነው። ፈላስፋ ጥቅጥቅ ባሉ የኃሳብ መንገዶች ነጉዶ ያገኘውን ሁሉ ሊያሰላስል የቆረጠ መርማሪ ነው፤ አንዳች የሙያ ሰገነትን እንዲቆናጠጥ የማይጠበቅ። በጥያቄ እና በፍተሻ ጉዞው መጨረሻ የሆነ ለምለም መስክ ባያገኝ ግድ የለውም፤ ጉዳዩ ጉዞው ነው። ከማሰቡ ነው እንጂ አስቦ በስተመጨረሻ ከሚደርስበት መደምደሚያ አይደለም፤ መጨረሻ ላይኖረው ይችላል።


በአንድ ሰው መቃብር ላይ የተጻፈ!


ወጣት ሳለሁ ምናቤ ገደብ በሌለው ወቅት ፥ ዓለምን ስለ መለወጥ አልም ነበር። እያደኩና እየበሰልኩ ስመጣ ግን ፥ ዓለምን መለወጥ እንደማልችል ተረዳሁ። ከዚያም ምኞቴን አጠር አደረኩና ሀገሬን ለመለወጥ ወሰንኩ። ነገር ግን እሱም የሚሳካ አልሆነም።


ወደ እድሜዬ መጨረሻ እየደረስኩ ስመጣ ፥ አንድ ሙከራ ለማድረግ ወሰንኩ፤ ይኽም የራሴን ቤተሰብ እና ለኔ ቅርብ የሆኑትን ለመለወጥ ወሰንኩ፤ እሱም አልሆነም።


በዚኽች ምድር ላይ የነበረኝ ቆይታ ሲገባደድ የመጨረሻዋ ሰዓት ላይ ፥  አልጋዬ ላይ ተጋድሜ ድንገት ይህንን  አስተዋልኩ፤

ራሴን ለውጬ ቢሆን ኖሮ ቤተ-ሰቤን መለወጥ እችል ነበር። ከዚያም ሀገሬን የተሻለች ማድረግ እችል ነበር። ማን ያውቃል ዓለምንም መቀየር እችል ይሆን ነበር!


እናስ?! እናማ ለውጥን ከራስህ ጀምር!

Comments

Popular posts from this blog

ከታሪክ ማህደር ክፍል 1

Seenaa Motummaa Jimmaa (kutaa 1ffaa)

The Untold Story of the Battle of Maqdala and the Struggle Between Emperor Tewodros and the Oromos